October 17, 2025
ዓምደ ሃይማኖት
5 ደቂቃ ንባብ
176 እይታዎች

በርቀት እና ኢ-ለርኒነግ መንፈሳዊ ትምህርት የተማሩ 500 ተማሪዎች ተመረቁ

በርቀት እና ኢ-ለርኒነግ መንፈሳዊ ትምህርት የተማሩ 500 ተማሪዎች ተመረቁ ።

( ዓ/ሃ/ሚ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም )

በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅ / ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የርቀት ትምህርት ማዕከል ስር በርቀት እና በበይነ መረብ ( ኢ-ርኒነግ) እንዲሁም በቅርንጫፍ   ለአንድ ዓመት ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዐት በዛሬው እለት  በደማቅ ሁኔታ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ተከናወነ ። የዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርትን ላለፉት 25 ዓመታት  በርቀት ትምህርት  በርካታ ምዕመናንን በማስተማር ያስመረቀ ሲሆን በዛሬው እለትም ተጨማሪ 421 ተማሪዎች በመደበኛ ርቀት ትምህርት፥ 68 በርቀት ከወልድያ ቅርንጫፍ ማእከል እና 11 በኢ- ለርኒንግ ተማሪዎች  በድምሩ 500 ተማሪዎች   መመረቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው መሰረታዊ የቤተክርስቲያን ታሪክ ማለትም፡-  ስለ ሥነ ፍጥረት ፣ ትምህርተ ሃይማኖት ፣ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ፣ ነገረ ክርስቶስ ፣ ነገረ ማርያም ፣ ነገረ ቅዱሳን ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ብሉይ ኪዳን ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አዲስ ኪዳን ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በሚሉ ዙሪያ በአጋዥ መጽሐፍ እና ማጠናከሪያ ትምህርት እና የምዘና ሥርዓት አጠናቀው መመረቃቸው ከርቀት ትምህረት ማዕከሉ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

በምርቃት ሥነ ሥርዐቱ ላይ  ርዕሰ ርዕሳን ቆሞስ አባ ተክለ ማርያም ባዬ የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ፥ ሊቀ ስዩማን ዘመነ ጽጌ  የገዳማችን ዋና ጸኃፊ ፥ መጋቤ ሐዲስ አባ ገብረ ማርያም እሸቴ የገዳማችን ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የርቀት ትምህርቱን ሌሎች ምእመናን በመማር ስለአንዲቷ እምነታቸው እና  ቤተ ክርስቲያናቸው ማወቅና በሕይወት መተርጎም እንደሚገባ ተገልጿል።  ምእመናንም በርቀት ትምህርት አልያም በኢ-ለርኒነግ ዘዴ  አመቺ በሆነላቸው መንገድ በቀጣይ ዙሮች ተመዝግበው አንዲማሩም ጥሪው ቀርቧል።

በማኅበራዊ ሚድያዎቻችን ይከተሉን

ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/AmdehaymanotSundayschool/

ዩትዩብ ፦ https://youtube.com/channel/UC_USHmHSlXg_-g0wwsPcQCg

ቲክ ቶክ፦ https://vm.tiktok.com/ZML9jVNJW/

ቴሌግራም፡ https://t.me/Amde_Haymanot_Sunday_School

ዓምደ ሃይማኖት

ዓምደ ሃይማኖት

መንፈሳዊ መምህር

Experienced financial educator with years of expertise in trading, investment strategies, and market analysis. Dedicated to empowering individuals with practical financial knowledge.