ዓላማችን

እውነተኛ የመንፈሳዊ እውቀት እንዲገነቡ፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያውቁ እና በሕይወትዎ በእምነት እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡

ራእያችን

ተደራሽ እና ጥራት ያለው የኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማቅረብ ብቁ እና መንፈሳዊ ትውልድ ማፍራት፡፡

እሴቶቻችን

የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቀኖና እና ትውፊት መጠበቅ፣ ታማኝነት፣ መንፈሳዊ ትጋት እና ለተማሪዎች ፍቅርና እንክብካቤ መስጠት፡፡

የትምህርት ዘርፎች

ከመጀመሪያ እስከ ብቁነት

የእኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪውን ከመጀመሪያ ደረጃ አንስቶ እስከ ከፍተኛ መንፈሳዊ እውቀት ያደርሳል፡፡ ሙከራ

ደረጃ 1

መሰረታዊ ትምህርት

የክርስትና መሠረቶች እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

የመንፈሳዊ ጉዞዎን ይጀምሩ፡፡ የኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ እምነት መሠረቶችን፣ የጸሎት ሕይወትን እና የቅዳሴን ሥርዓት ይማሩ፡፡

  • መሰረታዊ የሃይማኖት ትምህርት

  • የጸሎት እና የምስጋና ሥርዓት

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ

  • የቤተክርስቲያን ታሪክ

ደረጃ 2

መካከለኛ ትምህርት

የነገረ መለኮት እና የትርጓሜ ትምህርቶች

እውቀትዎን ያሳድጉ፡፡ የመጻሕፍት ትርጓሜ፣ ነገረ ድኅነት እና ሥነ ምግባርን በጥልቀት ይመርምሩ፡፡

  • ነገረ መለኮት (Theology)

  • የወንጌል ትርጓሜ

  • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

  • የአበው ታሪክ እና ትምህርት

ደረጃ

ከፍተኛ ትምህርት

የላቀ መንፈሳዊ አመራርና አገልግሎት

የላቀ የመንፈሳዊ እውቀት ደረጃ፡፡ የጥንታውያን መጻሕፍት ትምህርት፣ ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ አገልግሎት አመራር፡፡

  • የላቀ ነገረ ሃይማኖት

  • ስብከተ ወንጌልና አገልግሎት

  • የሊቃውንት መጻሕፍት ጥናት

  • የምስክር ወረቀትና ሰርተፊኬት

የትምህርት አሰጣጥ

እንዴት እናስተምራለን?

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከመንፈሳዊ ይዘቶች ጋር በማዋሃድ ትምህርቱን ምቹ፣ ሳቢ እና የማይረሳ እናደርገዋለን፡፡

የተብራሩ የጽሑፍ ማስታወሻዎች

ለማንበብ እና ለመረዳት ቀላል የሆኑ አጠቃላይ የመማሪያ ማስታወሻዎች፡፡

ዲጂታል መጻሕፍትና ማጣቀሻዎች

በምስል እና በሥርዓት የተዘጋጁ ጥራት ያላቸው የመንፈሳዊ መጻሕፍት አቅርቦት፡፡

የድምፅና ቪዲዮ ትምህርቶች

በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ ሊያደምጧቸው የሚችሉ የተሰናዱ የመምህራን ድምጾችና ቪዲዮዎች፡፡

የፈተናና ምዘና ሥርዓት

እውቀትዎን በየደረጃው የሚመዝኑ ፈተናዎች፣ ጥያቄዎች እና የውጤት ካርዶች፡፡

ለምን ይመርጡናል?

ላለፉት 25 ዓመታት መሰረታዊ ቤተክርስቲያናችንን ትምህርት በርቀት የማስተማር ልምድ ማካበታችን

ትክክለኛውን የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ትምህርት በዘመናዊና ምቹ መንገድ ያግኙ፡፡

በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምረው እውቅና በተሰጣቸው 5 መጻህፍት መሰረት አድርገን በምንሰጠው ትምህርት

በመንፈሳዊ ሕይወትዎ እና በእምነትዎ ላይ ጠንካራ እና የማያወላውል መሠረት ይገንቡ፡፡

የመምህራን እና የመደበኛ ሰራተኞች ጭምር ክትትል ማድረጋችን

በትምህርት ዝግጅታቸውና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው በተመሰከረላቸው መምህራን የሚሰጥ ትምህርት፡፡

ምቹ የኦንላይን ፕላትፎርም ማዘጋጀታችን

በቤትዎ፣ በሞባይልዎ ወይም በኮምፒውተርዎ በፈለጉት ሰዓት ያለምንም እንከን የመማር ነፃነት፡፡

የትምህርቱ ፍሬ

ኮርሶችን አጠናቀው ሲያልፉ ከምስክር ወረቀት የምንሰጥ መሆናችን

በአዲስ አበባ መሃል መገኘታችን

በአካል መጥተው ቲቶር ለመከታተል ወይንም ቢሮዋችን ለመጎብኘት አመቺ ቦታ ማለት ም4 ኮሎ ቤተ መንግስት ጎን መገኘታችን